የማህበሩ ዋና ገንዘብ /ካፒታል/ 298,153,000.00

                            የምዝገባ ቁጥር MT/AA/270011599/2004

ለብርሃን ኢንሹራንስ .. ባለአክስዮኖች  የተላለፈ የጉባኤ ጥሪ

የብርሃን  ኢንሹራንስ  አ.ማ. የባለአክሲዮኖች  12ኛ መደበኛ  እና 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ   ቅዳሜ  ታህሣሥ 13  ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት  ጀምሮ  አዲስ አበባ ፤ ካዛንቺስ  በሚገኘው ኢሊሊ ሆቴል ይካሔዳል ፡፡ ስለሆነም የኩባንያችን ባለአክሲዮኖች በሙሉ ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ /መንጃ ፍቃድ/ ፓስፖርት በመያዝ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪ ያቀርባል ፡፡

ሀ. የመደበኛ ጉባኤ አጀንዳ

  1. የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ ፤
  2. አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማጽደቅ ፤
  3. የዳይሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ 2022/23 ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥ ፤
  4. የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ 2022/23 የሂሳብ ሪፖርት ማድመጥ ፤
  5. ከዚህ በላይ በተራ ቁጥር 3 እና 4 ላይ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን ፤
  6. በተጓደሉ የቦርድ አባል ምትክ የተተኩትን ዳይሬክተር ሹመት ማጽደቅ ፤
  7. በ2015 ዓ.ም. በተደረገው የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ  በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተሰጠው ግብረ መልስ መሰረት ሰለተደረገው ማስተካከያ መግለጫ ማቅረብ ፤
  8. በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን ፤
  9. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ወርሃዊ አበልና ዓመታዊ ክፍያ መወሰን ፤
  10. የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ ፤

ለ. የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ

  1. አጀንዳውን ማጽደቅ ፤
  2. የማህበሩን ካፒታል ማሳደግ ፤
  3. የማኅበሩን መመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻል ፤
  4. የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ ፤

ማሳሰቢያ 

በጉባኤው ላይ ለመገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ፡-

  • ጉባኤው ከሚካሄድበት ቀን አስቀድሞ ባሉት ቀናት ውስጥ የኩባንያው ዋና መ/ቤት አድራሻ በሆነው በአዲስ አበባ ከተማ፤ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር አዲስ በሆነውና ወሎ ሰፈር ጋራድ ሲቲ ሴንተር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት አክስዮን አስተዳደር ክፍል በመገኘት የውክልና ፎርም/ቅጽ  በመሙላት ተወካይ በመወከል  ወይም ፤
  • በስብሰባው ለመገኘትና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ማስረጃ ያለው ተወካይ ዋናውን እና አንድ ፎቶ ኮፒ በጉባኤው ዕለት ይዞ እንዲቀርብ በማድረግ በወኪሎቻቸው አማካይነት መሳተፍ ይችላሉ ፡፡

 

ብርሃን ኢንሹራንስ .

የዳይሬክተሮች ቦርድ